ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶቹን ከኢትዮጵያ ውጭ ለማሻገር እና ገቢውን ለማሳደግ ያለመ አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶቹን ከኢትዮጵያ ውጭ ለማሻገር እና ገቢውን ለማሳደግ ያለመ አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አደረገ
ኩባንያው በዲጂታል ዘርፍ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማበረታታት እና የመንግሥትን የ10-ዓመት የልማት አጀንዳ በተለይም የዲጂታል መታወቂያ 2030ን ለማሳካት ያለመውን እቅድ በዋና ሥራ አስፈፃሚው ፍሬህይወት ታምሩ በኩል አስታውቋል።
“ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ” የወጠናቸው ቁልፍ ጉዳዮች፦
◻ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት 235.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት፣
◻ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ በሚቀጥለው ዓመት በ6% በማሳደግ 225.9 ሚሊየን ዶላር ማድረስ፣
◻ 327 አዳዲስ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን እንዲሁም ከ3.5 ሚሊየን በላይ የደንበኞች መጠቀሚያ መሳሪያዎችን ወደ ገበያ ማምጣት፣
◻ የደንበኞቹን ቁጥር አሁን ካለበት 83.2 ሚሊየን ወደ 88 ሚሊየን ማሳደግ፣
◻ የ4ጂ ተደረሠሽነትን 550 ከተሞችን በማካተት ወደ 85% ማሳደግ፤ በተጨማሪም የ5ጂ አገልግሎት በ10 ተጨማሪ ከተሞች በማስፋት የ5ጂ ጣቢያዎችን ቁጥር ከ315 ወደ 490 ከፍ ማድረግ፣
◻ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በሚያደርገው የቴሌኮም እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ኢንቨስትመንቶች ሀብቱን ከ332 ቢሊየን ብር ወደ 501 ቢሊየን ብር ለማሳደግ አቅዷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X