ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል አየር ማረፊያዎች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ
15:00 27.08.2025 (የተሻሻለ: 15:04 27.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል አየር ማረፊያዎች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል አየር ማረፊያዎች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ
ተቋሙ ከግል የበረራ ድርጅቶች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እየተወያየ ሲሆን በ2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች የሀገሪቱ የክልል አየር ማረፊያዎች ዓለም አቀፍ በረራ ማስተናገድ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።
እንደ ባለሥልጣኑ ማብራሪያ ከሆነ፦
የቱሪዝም ፍሰቱን ለመጨመር እንዲሁም የደንበኛውን እንግልት ለመቀነስ ከሚዛን ቴፒ -ጅማ - ጋምቤላ -አሶሳ እንዲሁም ከድሬደዋ- ሃረር -ባሌ ሮቤ የሚደረጉ የትስስር በረራዎችን፣
የሀገሪቱን የወጪ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ልማት ለመደገፍ ከባህር ዳር፣ መቀሌ እና ድሬደዋ የሚደረጉ በረራዎችን፣
የሃጂ ኡምራ ጉዞ፣ የኢየሩሳሌም፣ ገናን በላሊበላ እና ጥምቀትን በጎንደር የመንፈሳዊ ጉዞዎችን ለማስተሳሰር ታቅዷል፡፡
የክልል አየር ማረፊያዎችን ማስተሳሰሩ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለመሄድ የግድ አዲስ አበባን መርገጥ እንዳይኖርበት የሚያደርግ ነው መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X