ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነቴን ሰኔ 30፣ 2018 አውጃለሁ አለች
14:06 27.08.2025 (የተሻሻለ: 14:14 27.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነቴን ሰኔ 30፣ 2018 አውጃለሁ አለች
ሁሉም ክልልና የከተማ አስተዳደር ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚያስፈልገውን ሜትሪክ ቶን እህል እስከ ዞንና ወረዳ ድረስ እንዲይዝ እየተሠራ እንደሆነ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ክልሎች ለፌዴራል መጠባበቂያ የሚሆን ምርት አምርተው ለመስጠት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ውል ገብተዋል። ለዚህም ለቅድመ ፋይናንስ 3 ቢሊየን ብር ሊተላለፍላቸው መታቀዱን የኮሚሽኑን ኃላፊ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።
ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት 70 ከመቶ የሚሆነው ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሸፈነው በማህበረሰቡ ነው ማለቱንም ዘገባው አስታውሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X