ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ቁርጠኛ ነች - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
13:41 27.08.2025 (የተሻሻለ: 15:34 27.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ቁርጠኛ ነች - የክሬምሊን ቃል አቀባይ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ቁርጠኛ ነች - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
የዲሚትሪ ፔስኮቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦
▪ በዩክሬን ያለው ግጭት ውስብስብና በሩሲያ የተቀሰቀሰ አይደለም።
▪ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ለሚካሄደው አዲስ ድርድር ትክክለኛ ቀን አልተቆረጠም።
▪ የደህንነት ዋስትናዎች ለዩክሬን ገጭት መፍትሄ ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው።
▪ በፑቲን እና በትራምፕ መካከል በአላስካ የተካሄደው ውይይት ከፍተኛ ትርጉም ያለው እና አስፈላጊ ነበር።
▪ ሩሲያ ትራምፕ በዩክሬን ያለው ሁኔታ እንዲፈታ የሚያደርጉት የማሸማገል ጥረት እንደሚቀጥል ተስፋ ታደርጋለች፤ ጥረታቸውም አስፈላጊ እንደሆነ ታምናለች።
▪ በዩክሬን ጉዳይ ላይ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል የሚሠሩ ሥራዎች ውጤት እንዲያመጡ ለሕዝብ ይፋ ባልሆነ መንገድ መከናወን አለባቸው።
▪ ሩሲያ የአውሮፓ ሀገራት ወታደሮች በዩክሬን ግዛት ላይ ሊኖራቸው ስለሚችለው ተሳትፎ በተመለከተ በአውሮፓ የሚደረጉ ውይይቶችን በአሉታዊ መልኩ ትመለከታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X