የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ሰመራ መካሄድ ጀመረ

ሰብስክራይብ

የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ሰመራ መካሄድ ጀመረ

ፌስቲቫሉ የክልሉን ባሕላዊ የእርሻ ሥራ ወደ ዘመናዊ የግብርና ልምዶችና ክህሎቶች በመለወጥ ምርታማነትን ለመጨመር እና የቴምር ምርትን ለማሳደግ እድል ይሰጣል ሲሉ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ፌስቲቫሉን ትናንት ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡

የግብር ሚኒስትር ዲኤታ መለሰ መኮንን በበኩላቸው "ከአፋር በተጨማሪ እንደ ሶማሊያ፣ ጋምቤላ እና የኦሮሚያ ያሉ ክልሎች ያላቸው ምቹ የአየር ንብረት እና ለም መሬት ለቴምር እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል" ብለዋል፡፡

እሰከ ሀሙስ በሚቆየው ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል በቴምር ዘርፍ የተሠማሩ እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የከሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸር ኢኖቬሽን፣ ከሳዑዲ እና ሌሎች ሀገራትም በርካቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0