ናይጄሪያ ውስጥ የመንገደኞች ባቡር መስመሩን ሳተ፤ በአደጋው እስካሁን የተመዘገበ ሞት የለም

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ ውስጥ የመንገደኞች ባቡር መስመሩን ሳተ፤ በአደጋው እስካሁን የተመዘገበ ሞት የለም

  የአቡጃ-ካዱና የመንገደኞች ባቡር ሳይጠበቅ ሀዲዱን በመሳቱ መንገደኞች ከባቡሩ ለመውጣት ሲጣደፉ ግርግር መፈጠሩን የአካባቢው ሚዲያ ዘግቧል።

ተሳፋሪዎች ከተገለበጠው ባቡር ለመውጣት ሲሞክሩ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የናይጄሪያ የባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ካዮዴ ኦፔይፋ፤ የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና በአቅራቢያው የሚገኙ ሆስፒታሎች አስቀድመው በአደጋው ሥፍራ መሠማራታቸውን አስታውቀዋል።

“ሁሉንም ተሳፋሪዎች በሰላም ወደ አቡጃ ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ ነው፤ የደህንነት አካላትም አደጋው ወደ ተከሰተበት ሥፍራ ደርሰዋል” ብለዋል።

ከማህበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0