ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ የሱዳን ከተሞች የሰብዓዊ እርዳታ ማግኘት እንደጀመሩ ዩኒሴፍ አስታወቀ
19:41 26.08.2025 (የተሻሻለ: 19:44 26.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ የሱዳን ከተሞች የሰብዓዊ እርዳታ ማግኘት እንደጀመሩ ዩኒሴፍ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ የሱዳን ከተሞች የሰብዓዊ እርዳታ ማግኘት እንደጀመሩ ዩኒሴፍ አስታወቀ
በደቡባዊ ሱዳን ሁለት ከተሞች ከ120 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከወራት ከበባ እና እየተባባሰ በመጣው የምግብ እጥረት ምክንያት አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸው እንደነበር በድርጅቱ መግለጫ ተነቧል።
በተመሳሳይ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ክፍል በሚገኘው የሰሜን ዳርፉር ግዛት ግጭቱ እየተባባሰ መጥቷል። የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት (ኦቻ) በከበባ ውስጥ ባለችው የግዛቲቱ ዋና ከተማ አል ፋሽር፤ ጠለፋ እና ታጠቂዎች የሚፈፅሟቸውን ጥቃቶች ተከትሎ አንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ከተፈናቃዮች ካምፕ ሸሽተዋል ብሏል።
በሰሜን ዳርፉር በምትገኘው ሌላኛው ከተማ መሊት የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ግምገማዎች እንደሚያሳዩት ከሶስት ህጻናት አንዱ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ይሰቃያል።
ወሳኝ የእርዳታ አቅርቦቱን እንደሚቀጥል ቃል የገባው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ የደህንነት እጦት፣ የሎጂስቲክስ መሰናክሎች እና ከባድ የገንዘብ እጥረት ዋነኛ እንቅፋት እንደሆኑበት ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X