የካቲት 12 ሆስፒታል ለመጀመሪያ ግዜ በተሳካ ሁኔታ ሆድ ሳይከፈት የቀዶ ጥገና አከናወነ
19:22 26.08.2025 (የተሻሻለ: 19:24 26.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የካቲት 12 ሆስፒታል ለመጀመሪያ ግዜ በተሳካ ሁኔታ ሆድ ሳይከፈት የቀዶ ጥገና አከናወነ
🩻 ትንንሽ ቀዳዳዎችን በመፍጠር ካሜራና የቀዶ ጥገናና መሳሪያዎችን በመክተት የሚከናወነው ህክምና፤ 102 ዓመት ላስቆጠረው የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ፈር ቀዳጅ ነው።
ህክምናው በ30 ዓመት ዕድሜ ታካሚ ሴት ኩላሊት እና ጉበት መካከል የተገኘን እጢ ለማስወገድ የተደረገ ነው።
🩺 የካቲት ሆስፒታል ለቀዶ ጥገናው የሚያስፈልጉ ሀርሞኒክ ወይም ላይጌቸር የተባሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች ባይኖሩትም ሁለት ሰዓት በፈጀ ቀዶ ሕክምና፣ በጥቂት ቀዳዳዎች እና ለአይን በማይታዩ ጠባሳወች እጢውን ማስወገድ ችሏል።
ህክምናው ሆስፒታሉ ዘመኑን የዋጀ ቀዶ ጥገና ለማካሄድ የሚያስችል አቅም እና ባለሙያዎችም እንዳሉት ያሳየ ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X