አፍሪካ ‘በሰልፉ መጨረሻ ከመሆን’፤ የራሷን የክትባት ማምረቻ ማቋቋም አለባት ሲሉ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ
17:34 26.08.2025 (የተሻሻለ: 17:44 26.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ ‘በሰልፉ መጨረሻ ከመሆን’፤ የራሷን የክትባት ማምረቻ ማቋቋም አለባት ሲሉ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ ‘በሰልፉ መጨረሻ ከመሆን’፤ የራሷን የክትባት ማምረቻ ማቋቋም አለባት ሲሉ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ
“በኮቪድ ወቅት የኮቪድ ክትባቶች ማከማቻ መጋዘኖችን ለመክፈት ብዙ ጊዜ ወስዷል። ፈጣን ዲፕሎማሲ ባለመኖሩ አላግባብ የሰው ህይወት ነጥቆናል” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ሀገራት፦
ከአፍሪካ ውጭ ባሉ ሀገራት ላይ ያላቸውን የመድኃኒት አቅርቦት ጥገኝነት እንዲያስወግዱ፣
እኩልነትን ለማስፈን የጤና ዲፕሎማሲን እንዲያጠናክሩ፣
ለወረርሽኞች ምላሽ ለመስጠት በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ጠንካራ የመቋቋም አቅም እንዲገነቡ አሳስበዋል።
ጤና ለክልላዊ ንግድና ኢንዱስትሪ መነሳሳት መንስኤ እንዲሆን አበክረው አሳስበዋል።
አህጉሪቱ አሁንም በከፍተኛ የእናቶችና ህፃናት ሞት፣ በወባና በኤችአይቪ የታየው መሻሻል መገታት እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቁጥር በመጨመሩ እየተፈተነች እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ ገብረኢየሱስ አስጠንቅቀዋል።
75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉባኤ በሉሳካ የተከፈተ ሲሆን በአዳዲስ የጤና ተነሳሽነቶች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X