ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና መስፈርት አዘጋጀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና መስፈርት አዘጋጀች
ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና መስፈርት አዘጋጀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.08.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና መስፈርት አዘጋጀች

ሀገሪቱ አሁን ላይ በመስኖ ማልማት ከምትችለው 42 ሚሊየን ሄክታር መሬት 2 ሚሊየን የሚሆነውን ብቻ በመስኖ እያለማች ትገኛለች።

ይህን ክፍተት ለመሙላት አልሟል የተባለው አዲስ የአሠራር መመሪያ፤ በመንግሥታቱ ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲሁም በአዲስ አበባና አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ትብብር የተዘጋጀ ነው።

ሰነዱ በአዋጭነት ጥናት ላይ የተመሠረተ የመስኖ ፕሮጀክት የልማት ሥራዎችን በታወቀ የአሠራር ሥርዓት ማከናወን የሚያስችል አካሄድ መዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የመስኖ ልማት የፕሮጀክቶች ጥራት ማስጠበቂያ ሰነዱ፤ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተነግሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0