"ስፑትኒክ አፍሪካ ለምዕራባውያን ሚዲያዎች አድሎዓዊነት መድኃኒት ነው" - የቡርኪና ፋሶ የባሕል ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

"ስፑትኒክ አፍሪካ ለምዕራባውያን ሚዲያዎች አድሎዓዊነት መድኃኒት ነው" - የቡርኪና ፋሶ የባሕል ሚኒስትር

በ 'ስፓስካያ ታወር ወታደራዊ የሙዚቃ ፌስቲቫል' ላይ የሀገራቸውን ሙዚቀኞች ለመደገፍ ሞስኮ የተገኙት የቡርኪና ፋሶ የባሕል ሚኒስትር ፒንግድዌንዴ ጊልበርት ኦዌድራጎ፤ በመረጃ ተዓማኒነት እንዲሁም በአፍሪካ ጉዳዮች ዙሪያ ስለሚሠሩ ዘገባዎች ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ "አፍሪካውያን በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ የቡርኪና ፋሶ ሕዝብ ሙሉ ሉዓላዊነትን ይፈልጋሉ። ስለ ሉዓላዊነት ስንናገር፤ የመገናኛ ብዙኃን ተዓማኒነትን ጭምርም ማለታችን ነው" ብለዋል።

አክለውም አንዳንድ ምዕራባውያን ሚዲያዎች "አድሎዓዊ መሆናቸውን አሳይተዋል" ያሉት ሚኒስትሩ፤ በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ ላይ ትልቅ መሻሻል ቢኖርም "ሁሉንም ነገር ጥቁር አድርገው ይስላሉ" ብለዋል። ይህ ደግሞ የቡርኪና ፋሶ ሕዝብ ከእነዚህ የመረጃ ምንጮች እንዲርቅ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል።

"ዛሬ እኛ የምንፈልገው ለሕዝብ እውነተኛ መረጃ የሚሰጡ ትክክለኛ እና ተዓማኒ የሆኑ ሚዲያዎችን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህ የሚዲያ ሥነ -ምህዳር ውስጥ፤ ስፑትኒክ አፍሪካ አስተማማኝ እና ሚዛናዊ ዘገባዎችን ለማቅረብ ባለው ቁርጠኝነት ጎልቶ ይታያል። ይህ የመረጃ ምንጭ በዘገባዎቹ ላይ "ትክክለኛ እውነታን" ያሳያል ብለዋል።

"አሁን ላይ መረጃ ኃይለኛ መሣሪያ ነው፡፡ እውነትን ያልያዘ ሲሆን ደግሞ አውዳሚ ይሆናል" በማለት ሚኒስትሩ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0