ግብጽ "የታላቋ እስራኤል ቅዠት" እንዲተገበር አትፈቅድም ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገሩ
14:04 26.08.2025 (የተሻሻለ: 14:14 26.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱግብጽ "የታላቋ እስራኤል ቅዠት" እንዲተገበር አትፈቅድም ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግብጽ "የታላቋ እስራኤል ቅዠት" እንዲተገበር አትፈቅድም ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገሩ
ሚኒስትሩ ባድር አብደላቲ በእስላማዊ ትብብር ድርጅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ፍላጎት የሥልጣን እብሪተኝነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
◻ አክለውም ግጭቱን የበለጠ የሚያባብስ፣ መጠኑን የሚያሰፋ እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ሕዝቦች በሰላም አብረው እንዳይኖሩ የሚከለክል ነው ሲሉ የግብፁ ከፍተኛ ዲፕሎማት አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሐምሌ ወር መጀመሪያ "ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ተልዕኮ" ላይ መሆናቸውን የገለፁት ኔታንያሁ፤ ሁሉንም የተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች እና የአጎራባች ሀገራት ግዛቶችን የመጠቅለል ዕቅድ የሚያካትተውን የ "ታላቋ እስራኤል" ራዕይ በብርቱ እንደሚደግፉ ተናግረው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X