የሞስኮ ውድድር አፍሪካ ብቁ ስኬተሮች የሏትም የሚለውን እሳቤ የሰበረ ነው - የኢትዮጵያ ልዑክ አባል

ሰብስክራይብ

የሞስኮ ውድድር አፍሪካ ብቁ ስኬተሮች የሏትም የሚለውን እሳቤ የሰበረ ነው - የኢትዮጵያ ልዑክ አባል

በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ የሚገኘው የ2025 የግራንድ ስኬት ቱር የኢትዮጵያ ልዑክ አባል አቤኔዘር ተመስገን፤ ዝግጅቱ ለአፍሪካ የስኬት ስፖርት አፍቃሪያን ሰፊ ዕድል የሰጠ መሆኑን ይገልጻል።

"ዓለም ላይ የተለያዩ የስኬት ዝግጅቶች ቢካሄዱም፤ ለአፍሪካ ስኬተሮች ግን ብዙ ቦታ የላቸውም። ምክንያቱም አፍሪካ ውስጥ የሥልጠና መሠረተ ልማቱ የተሟላ ባለመሆኑ በቂ አይደሉም የሚል እሳቤ በመኖሩ ነው። ይሄ ዝግጅት ግን ይህን አረዳድ የቀየረ ነው" ብሏል።

አቤኔዘር ተመስገን ይህ ግዙፍ ውድድር በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚካሄድበት አግባብ ላይ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ጋር ንግግሮች እየተካሄዱ መሆኑንም ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0