የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ሞተሮችን የአፈፃፀም ብቃት ወደ ፋብሪካ ደረጃ የሚመልስ የጥገና አገልግሎት ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ሞተሮችን የአፈፃፀም ብቃት ወደ ፋብሪካ ደረጃ የሚመልስ የጥገና አገልግሎት ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ሞተሮችን የአፈፃፀም ብቃት ወደ ፋብሪካ ደረጃ የሚመልስ የጥገና አገልግሎት ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ሞተሮችን የአፈፃፀም ብቃት ወደ ፋብሪካ ደረጃ የሚመልስ የጥገና አገልግሎት ይፋ አደረገ

Leap-B1 ተብሎ የሚጠራው የጥገና አገልግሎት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እና ከአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር አስፈላጊውን የጥራት ማረጋገጫ እንደተሰጠው አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በስኬቱ ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀው "ይህ አቅም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሊፕ-1ቢ ሙከራ አቅም ካላቸው በጣም ጥቂት ተቋማት መካከል አንዱ ያደርገዋል። የጥገና፣ እድሳት እና ማሻሻያ አገልግሎታችንን ለማስፋት እና ለማሳደግ በምናደርገው ጉዞ ታሪካዊ ቀን ነው" ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና፣ የእድሳት ማዕከልና ወርክሾፖችን በቅርቡ ማስመረቁ ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0