ለአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሉዓላዊ ተስፋ የሰነቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሉዓላዊ ተስፋ የሰነቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት
ለአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሉዓላዊ ተስፋ የሰነቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.08.2025
ሰብስክራይብ

ለአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሉዓላዊ ተስፋ የሰነቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት

የ24 ዓመቱ በቃሉ ተመስገን የኢኮኖሚክስ ተማሪ እና የብዝኃ ቋንቋ የኤአይ ሥርዓት ተባባሪ መሥራች ነው፡፡ እሱ እና ሁለት የቡድን አጋሮቹ ለኢትዮጵያውያን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ተደራሽነት ችግርን የሚቀርፍ “ረስት” የተሰኘ የዲጂታል መድረክ አበልጽገዋል፡፡

በቃሉ በቂ የመረጃ ክምችት (ዳታ) ለሌላቸው ቋንቋዎች ክፍት መረጃ ማከማቻዎች መገንባት አለባቸው ብሏል፡፡

“እንደ አማርኛ፣ ስዋሂሊ እና አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ቋንቋዎች በማሽን መማሪያ እና በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምህዳሮች ውስጥ ዝቅተኛ ግብዓት ያላቸው ቋንቋዎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ቋንቋዎች ብዙ ዳታ የለም።”

ከሌሎች ሀገራት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ፈጠራ ጥገኝነት ለመላቀቅ፣ ተጠቃሚዎች በቀላሉ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ አማራጮችን በማቅረብ ዳታ ማከማቸት እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

“ለዚህ ደግሞ በዘርፉ መሠረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግን የመሳሰሉ ተነሳሽነቶችን በማበረታታት፤ የአፍሪካ ሀገራት በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ዘርፍ ሉዓላዊ መሆን ይችላሉ” ሲል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0