በዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ትዕዛዝ በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ላይ የቦምብ ጥቃት ልትፈፅም የነበረች ሴት ክራይሚያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች
12:49 25.08.2025 (የተሻሻለ: 12:54 25.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ትዕዛዝ በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ላይ የቦምብ ጥቃት ልትፈፅም የነበረች ሴት ክራይሚያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ትዕዛዝ በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ላይ የቦምብ ጥቃት ልትፈፅም የነበረች ሴት ክራይሚያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች
የታሰረችው ሴት በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አዶ ውስጥ የተደበቀ ቦምብ ወደ ሩሲያ ደህንነት ቢሮ (ኤፍኤስቢ) ይዛ ስትሄድ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ተገልጿል።
ሴትየዋ በስልክ አጭበርባሪዎች የተሰረቀባትን ገንዘብ ለመመለስ ጥረት እያደረገች እንደነበርና በዚህም ሂደት ወደ ሽብር ተግባር እንድትገባ እንደተታለለች ኤፍኤስቢ ገልጿል።
ባለፈው ግንቦት የሩሲያ ደህንነት መርማሪ ነኝ ያለ የኤስቢዩ አባል፤ በአሸባሪነት የተመዘገበ አንድ የዩክሬን ዜጋ በእሷ ስም ብድር ወስዶ ገንዘቡን ለዩክሬን ጦር እንዳስተላለፈ እንደነገራት ኤፍኤስቢ አስታውቋል፡፡
"በወንጀል ላለመጠየቅ በወንጀለኞቹ መመሪያ መሠረት ከ3 ሚሊየን ሩብል በላይ የሚሆን ብድር ወስዳለች...በኋላም የዩክሬናውያኑን ትዕዛዝ በመቀበል ወደ ክራይሚያ ተጉዛለች" ሲል መግለጫው አክሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X