ቡርኪና ፋሶ በቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈውን የፀረ-ወባ ፕሮጀክት በደህንነት ስጋት ምክንያት አቋረጠች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቡርኪና ፋሶ በቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈውን የፀረ-ወባ ፕሮጀክት በደህንነት ስጋት ምክንያት አቋረጠች
ቡርኪና ፋሶ በቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈውን የፀረ-ወባ ፕሮጀክት በደህንነት ስጋት ምክንያት አቋረጠች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2025
ሰብስክራይብ

ቡርኪና ፋሶ በቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈውን የፀረ-ወባ ፕሮጀክት በደህንነት ስጋት ምክንያት አቋረጠች

"ሁሉም ናሙናዎች ጥብቅ በሆነ መመሪያ መሠረት ይወገዳሉ" ሲል የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

“ታርጌት ማላሪያ” የወባ በሽታን ማስተላለፍ የማይችሉ ትንኞችን ለማራባት የሚሠራ በኩባንያ የሚተዳደር የምርምር ማኅበር ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን ትንኞች የለቀቀው በጎርጎሮሳውያኑ 2019 ነው፡፡ ከእገዳው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎም አሰራጭቶ ነበር፡፡

በቡርኪና ፋሶ የባዮቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር ጥምረት የሚመሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች፣ ይህንን ተነሳሽነት አደገኛ፣ ግልጽ ያልሆነ እና በጣም ጎጂ ነው ሲሉ ተቃውመውታል። በሰው ጤና እና በሥነ-ምኅዳሮች ላይ ሊተነበዩ የማይችሉ እና የማይቀለበሱ ተጽእኖዎች እንዳሉትም አስጠንቅቀዋል።

ተቺዎች፣ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው ትንኞች ዝርያዎች መነሻ የአውሮፓ ቤተ ሙከራዎች መሆኑን በመጠቆምም፣ ፕሮጀክቱን የሳይንሳዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ነው በማለት ይከስሳሉ፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0