ፔንታጎን ከፀደይ መጨረሻ ጀምሮ ኪዬቭ ሩሲያን ለማጥቃት የረዥም ርቀት ጦር መሣሪያዎችን እንዳትጠቀም ማገዱ ተዘገበ
18:40 24.08.2025 (የተሻሻለ: 18:44 24.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፔንታጎን ከፀደይ መጨረሻ ጀምሮ ኪዬቭ ሩሲያን ለማጥቃት የረዥም ርቀት ጦር መሣሪያዎችን እንዳትጠቀም ማገዱ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፔንታጎን ከፀደይ መጨረሻ ጀምሮ ኪዬቭ ሩሲያን ለማጥቃት የረዥም ርቀት ጦር መሣሪያዎችን እንዳትጠቀም ማገዱ ተዘገበ
የረዥም ርቀት መሣሪያዎች ለጥቃት የመጠቀም የአሜሪካ ክልከላ፣ የዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻን እየገደበ ነው ሲል ባለሥልጣናትን ጠቅሶ የአሜሪካ ጋዜጣ ዘግቧል።
በወራት ውስጥ አንዴ፣ ኪዬቭ ወደ ሩሲያ ዘልቃ ለማጥቃት የሠራዊት ስልታዊ የሚሳይል ሥርዓት(ኤቲኤሲኤማኤስ) ሚሳኤሎችን ለመጠቀም ሞክራ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሙከራ በአሜሪካ መከልከሉን ጽሑፉ ጠቁሟል፡፡
ክልከላዎቹ የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ “ስቶርም ሻዶው” የተሰኙ ክሩዝ ሚሳኤሎችንም እንደሚያካታቱ ጋዜጣው አክሏል፡፡
ሩሲያ ለዩክሬን የጦር መሣሪያዎችን ማቅረብ እልባቱን እንደሚያደናቅፍ እና የኔቶ ሀገራትን ግጭቱ ውስጥ በቀጥታ እንደሚያሳትፍ በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ድግሞ፣ ወደ ኪዬቭ የሚደረግ ማንኛውም የጦር መሣሪያ ጭነት ለሩሲያ ሕጋዊ ዒላማ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X