ከኢትዮጵያ የወጡ ቅርሶችን ለማስመለስ ልየታ እየተደረገ ነው ተባለ
17:25 24.08.2025 (የተሻሻለ: 17:34 24.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከኢትዮጵያ የወጡ ቅርሶችን ለማስመለስ ልየታ እየተደረገ ነው ተባለ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው በተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን ለማስመለስ የት ቦታ እና ማን ጋር ምን አይነት ቅርስ ይገኛል የሚለውን የመለየት ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ከጨረታ እንዲወርዱ በማድረግ ለማስመለስ እንደሚሠራም የተገለፀ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት፦
🟠 የአፄ ቴዎድሮስ ጋሻ፣
🟠 የራስ ደስታ ዳምጠው ካባ፣
🟠 የኢትዮጵያ ኮከብ ኒሻን እና
🟠 ሌሎች ከጨረታው ወርደው መመለሳቸውን በማሳያነት አንስተዋል።
በቅርስ ማስመለስ ስራ ላይ የብሔራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X