ዩክሬን እና የአውሮፓ ሕብረት ፑቲን እና ትራምፕ በአላስካ የተወያዩባቸውን በተለይም የደህንነት ዋስትና ጉዳይን ለማጣመም እየሞከሩ ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ዩክሬን እና የአውሮፓ ሕብረት ፑቲን እና ትራምፕ በአላስካ የተወያዩባቸውን በተለይም የደህንነት ዋስትና ጉዳይን ለማጣመም እየሞከሩ ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ለስብሰባው የሰጡት ምላሽ፣ የቅርቡ በዋሽንግተን ያደረጉት ስብሰባ እና ቀጥለው የመጡ እርምጃዎች ሰላም እንደማይፈልጉ ያመለክታሉ ሲሉ ለአሜሪካ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
▪ፑቲን እና ትራምፕ በአላስካ የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ ተግባራዊ እርምጃዎች እና አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
▪የሩሲያን ጥቅም ያገናዘበ የዩክሬን የደህንነት ዋስትናዎች ላይ መግባባት ሊኖር ይገባል፡፡
▪በዩክሬን ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ግቦች ለማሳካት፣ ሩሲያ ከሀገሪቱ የሚመጡትን ሁሉንም የደህንነት ስጋቶች ማስወገድ አለባት።
▪ሩሲያ በግዛቶች ላይ ፍላጎት የላትም፤ ሆኖም በዶንባስ እና ኖቮሮሲያ የሚኖሩ ሰዎች እጣ ፈንታ ያሳስባታል፡፡
▪ሞስኮ ትራምፕን ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቃቸውን ታከብራለች፤ ፑቲን የሩሲያን ጥቅም በማስጠበቃቸው እንደሚያከብሯቸው የሚያምኑበት ምክንያት አለ፡፡
▪ዘሌንስኪ አሁኑ ላይ፣ ጊዜ ሲደርስ(የስምምነት) ዩክሬንን ወክለው ማንኛውንም ሕጋዊ ሰነድ ለመፈረም ቅቡልነት የላቸውም።
▪ሩሲያ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከዩክሬን ጦር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ቦታዎች ሆን ብላ ዒላማ አላደረገችም፡፡
▪የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን በኢስታንቡል ተገናኝተዋል እናም የተለዩ ወታደራዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮችን ላይ መወያየታቸውን ይቀጥላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X