ምዕራባውያን ሰርቢያን ወደ ኔቶ በመቀላቀል የ1999 የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂነት እንዲነሳላቸው ይፈልጋሉ
14:07 24.08.2025 (የተሻሻለ: 14:14 24.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራባውያን ሰርቢያን ወደ ኔቶ በመቀላቀል የ1999 የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂነት እንዲነሳላቸው ይፈልጋሉ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ሰርቢያን ወደ ኔቶ በመቀላቀል የ1999 የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂነት እንዲነሳላቸው ይፈልጋሉ
በሰርቢያ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ቦትሳን-ካርቼንኮ፣ ምዕራባውያን ሰርቢያን ወደ ኔቶ ለማስገባት የሚሹት የ1999ኙን* የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂነትን ለመፋቅ ጭምር መሆኑን ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
"አመክንዮአቸውን እናውቃለን። የአውሮፓ ሕብረት አባልነት፣ የኔቶ አባልነት፤ ተያይዘው የሚመጡ ሳይነጣጠሉ የሚሄዱ ሁለት ነገሮች ናቸው" ብለዋል።
ኔቶ ዩጎዝላቪያ ላይ የፈፀመው ወረራ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ይሁንታ ሳያገኝ የተደረገ ነው፡፡ የኔቶ ቦምብ ጥቃት 87 ሕጻናትን ጨምሮ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ እንዲሁም የ100 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጉዳት አድርሷል። ሐኪሞች የካንሰር በሽታዎች እንዲጨምሩ ምክንያት የሆነውን የዩራኒየም ብናኝ ተጽእኖዎችን ሲመዘግቡ ነበር፡፡
*ኔቶ መጋቢት 1999 (1991 ዓ.ም) ኦፕሬሽን አላይድ ፎርስ ባለው የ78 ቀናት የቦምብ ጥቃት ዘመቻ፣ በዩጎዝላቪያ ኮሶቮ የሚገኙ የሰርቢያ ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን እና የሲቪል አካባቢዎችን ያወደመበት ጥቃት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X