በ2019 ዓ.ም የ1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስገባ የሚጠበቀው የኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ

© telegram sputnik_ethiopiaበ2019 ዓ
በ2019 ዓ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2025
ሰብስክራይብ

በ2019 ዓ.ም የ1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስገባ የሚጠበቀው የኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካ በሚቀጥለው ዓመት በግማሽ አቅሙ ማምረት እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡

“የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ነው፡፡ ... የክልሉን ሰፊ የወርቅ አቅምም ያሳያል። ከባለፈው ዓመት ጉብኝታችን በኋላ ያየነው እድገት የሚበረታታ ነው። ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በሚጠናቀቅበት ጊዜ በጎ ተጽዕኖው በመላው ክልሉ የሚታይ ይሆናል።” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ ስለ ፋብሪካው ከተናገሩት፦

በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ የወርቅ ፋብሪካ ይሆናል፡፡

ከ20 ኪሎ ሜትር ራዲየስ በላይ ቦታ ይዟል፡፡

ሦስት ግድቦች አሉት፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩበት የመኖሪያ ካምፕ የያዘ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ወርቅ በራሷ አቀነባብራና አምርታ መሸጥ ያስችላታል፡፡

ዐቢይ “ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።” ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበ2019 ዓ
በ2019 ዓ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0