የጋዛ ቀውስ አሁናዊ መረጃዎች
በእስራኤል አርብ በፍልስጤም ግዛት ላይ በፈፀመችው የቦምብ ድብደባ ቢያንስ 71 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 37ቱ በጋዛ ከተማ የተገደሉ ናቸው (ሚዲያ)
የእስራኤል በጋዛ ከተማ ሼክ ራድዋን ሰፈር በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ 12 ሰላማዊ ዜጎችን ሕይወታቸውን አጥተዋል (የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)
ቢያንስ በ64 አጋጣሚዎች፣ በጋዛ መጋጠሚያ እርዳታ ሲፈልጉ የነበሩ ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች በእስራኤል ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል (በፎረንሲክ አርክቴክቸር እና የዓለም የሰላም ፋውንዴሽን የተተደረገ የጋራ ምርመራ)
በረሃብ እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 112 ሕጻናትን ጨምሮ 273 ደርሷል (የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)
ዩኒሴፍ በዚህ የረሃብ ሁኔታ ውስጥ በጋዛ "እውነተኛ የሕጻናት ኅልውና ቀውስ" አለ ብሏል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ጋዛ የዓለም አምስተኛው የተረጋገጠ መጠነ ሰፊ ድርቅ እያስተናገደች መሆኗን ገልጿል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ምርኮኞችን ለማስፈታት እና ጦርነቱን ለማቆም የቅርብ ጊዜውን የተኩስ አቁም ሃሳብን ተከትሎ ንግግር እንዲጀመር አዝዘዋል (ይህም በኳታር እና በግብጽ አደራዳሪነት በሃማስ ተቀባይነት ያገኘ ስምምነት ነው፡፡ )
ኔታንያሁ በቅርብ ቀናት ውስጥ ጋዛ ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንዲጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

