ደቡብ ሱዳን በዓለም አቀፍ የእርዳታ ቀነሳ ምክንያት ቀጣይ ትውልዷን የማጣት ስጋት እንደተጋረጠባት የሕጻናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ ሱዳን በዓለም አቀፍ የእርዳታ ቀነሳ ምክንያት ቀጣይ ትውልዷን የማጣት ስጋት እንደተጋረጠባት የሕጻናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ
ደቡብ ሱዳን በዓለም አቀፍ የእርዳታ ቀነሳ ምክንያት ቀጣይ ትውልዷን የማጣት ስጋት እንደተጋረጠባት የሕጻናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.08.2025
ሰብስክራይብ

ደቡብ ሱዳን በዓለም አቀፍ የእርዳታ ቀነሳ ምክንያት ቀጣይ ትውልዷን የማጣት ስጋት እንደተጋረጠባት የሕጻናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ

እንደ የሕጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ቺልድረን) መረጃ፣ አሁን ላይ ከ2 ሚሊዮን በላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ሕጻናት ወሳኝ ሕክምና ማግኘት አልቻሉም፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ እና 1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲሰደዱ ያደረገው የሱዳን ግጭት ሁኔታውን ማባባሳቸውን የረድኤት ድርጅቱ ገልጿል።

የእርዳታ ቅነሳው በጤና፣ በትምህርት እና የቅድመ ልጅነት ትምህርት ማዕከላት መዝጋትን ጨምሮ የሕጻናት ጥበቃ አገልግሎቶች ላይ አስከፊ ተጽእኖ እንዳለው በሕጻናት አድን ድርጅት የካናዳ ዋና ሥራ አስፍጻሚ በጁባ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚሆነው የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ቀድሞም ቢሆን የሰብአዊ እርዳታ የሚፈልግ ሲሆን፣ የስደተኞች እና የተመላሾች መጉረፍ አሁን ባለው የእርዳታ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ነው ሲሉ የሕጻናት አድን ድርጅት ስዊዘርላንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገልጸዋል፡፡

ይህ ቀውስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና በሕጻናት ማኅበራዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑን ያስጠነቀቀው የሕጻናት አድን ድርጅት፣ ሀገሪቱ በ2011 ከሱዳን ከተገነጠለች በኋላ ያስመዘገበችውን ልማታዊ እድገት ሊቀለብስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0