ኢትዮጵያ ከዘንድሮው መኸር ከ672 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ትጠብቃለች
16:13 23.08.2025 (የተሻሻለ: 16:14 23.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከዘንድሮው መኸር ከ672 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ትጠብቃለች
እንደ ሀገር እስካሁን 19 ሚሊዮን ሔክታር መሬት መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኢሳያስ ለማ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
3.3 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በስንዴ ዘር መሸፈኑ የተገለፀ ሲሆን 2.1 ሚሊዮን ሔክታሩ በክላስተር (ኩታ ገጠም) የታረሰ ነው ተብሏል፡፡በአጠቃላይም በመኸር እርሻ 176 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢሳያስ ጠቅሰዋል፡፡
መሪ ሥራ አስፈፃሚው፣ በአሁኑ ወቅት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ከሆኑ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የሀገሪቷ ክፍል ዘር መዝራት ተጠናቅቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X