የናይጄሪያ የጉዞ እና የጉብኝት ወኪል ፊንችግሎው ሆሊዴይስ ቱሪዝምን ለማነቃቃት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከኢትዮጵያ ሆሊዴይስ ጋር አጋርነት ፈጠረ
15:05 23.08.2025 (የተሻሻለ: 06:34 24.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ የጉዞ እና የጉብኝት ወኪል ፊንችግሎው ሆሊዴይስ ቱሪዝምን ለማነቃቃት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከኢትዮጵያ ሆሊዴይስ ጋር አጋርነት ፈጠረ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ የጉዞ እና የጉብኝት ወኪል ፊንችግሎው ሆሊዴይስ ቱሪዝምን ለማነቃቃት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከኢትዮጵያ ሆሊዴይስ ጋር አጋርነት ፈጠረ
የድርጅቱ የቢዝነስ ኃላፊ ኦሉዋሴውን አፎላቢ፣ ናይጄሪያውያን ከተለመዱት የጉዞ መዳረሻዎቻቸው እየራቁ በመሆኑ ኢትዮጵያ በአኅጉሪቱ በጣም ማራኪ ገና ያልደረሰባቸውን መዳረሻዎችን እንደምታቀርብ ጠቁመዋል፡፡
"በጥንቃቄ የተመረጡ የጉብኝት ጥቅሎችን ከቀልጣፋ የቪዛ አሠራር ጋር በማቅረብ መሰናክሎችን እያስወገድን፣ ተደራሽነትን እያሳደግን እና የኢትዮጵያን የበለጸገ የባሕል ቅርስና የብዝኃ ቱሪዝም መስህቦችን ለናይጄሪያ ገበያ እያሳየን እንገኛለን።"
የትብብሩ ዋና ዋና ትኩረቶች ውስጥ፦
🟠 በናይጄሪያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ቱሪዝም ማነቃቃት፣
🟠 የንግድ ዕድሎችን ማሳደግ እና
🟠 የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያ ሥራ አስኪያጅ ፍሬሕይወት መኮንን በበኩላቸው፣ “ናይጄሪያ በአፍሪካ ካሉ በጣም አስፈላጊ ገበያዎቻችን አንዷ ስትሆን ከፊንችግሎው ሆሊዴይስ ጋር ያደረግነው ትብብር ይህንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋል” ማለታቸውን የናይጄሪያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X