የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመሮች ግንባታ ሊጀምር ነው ተባለ
13:32 23.08.2025 (የተሻሻለ: 13:34 23.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመሮች ግንባታ ሊጀምር ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመሮች ግንባታ ሊጀምር ነው ተባለ
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ በ2013 ዓ.ም በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ግንባታቸው ተቋርጠው የነበሩትን የባቡር መንገዶች ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችሉ ግምገማዎች ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ከሰሜን ጋር ለማገናኘት የተነደፉት የባቡር መስመሮቹ፦
የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር፣
የሐራ ገበያ - መቀሌ 268 ኪሎ ሜትር ርዝመት አላቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹ፣ የቻይና የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በአብዛኛው በውጭ ብድር የሚሠሩ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በዓመቱ ውስጥ ከግንባታ ፕሮጀክቶች እና ከሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች 710 ሚሊዮን ብር ገቢ ቢያገኝም፣ ከባቡር ሐዲድ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በውጭ ዕዳ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ግምገማው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X