የጋዛ ረሃብ፡ ‘ነገሮችን ባሉበት ከተውናቸው፣ ኃያል የሰብአዊ ቀውስ ወጀብ እንጋፈጣለን’

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጋዛ ረሃብ፡ ‘ነገሮችን ባሉበት ከተውናቸው፣ ኃያል የሰብአዊ ቀውስ ወጀብ እንጋፈጣለን’
የጋዛ ረሃብ፡ ‘ነገሮችን ባሉበት ከተውናቸው፣ ኃያል የሰብአዊ ቀውስ ወጀብ እንጋፈጣለን’ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.08.2025
ሰብስክራይብ

የጋዛ ረሃብ፡ ‘ነገሮችን ባሉበት ከተውናቸው፣ ኃያል የሰብአዊ ቀውስ ወጀብ እንጋፈጣለን’

“ይህ ረሃብ፣ የእርዳታ አቅርቦትን በመዝጋት እና የተባበሩት መንግሥታት ምግብ እንዳያከፋፍል በመከልከል እስራኤል የፈጠረችው ሰው ሠራሽ ቀውስ ነው” ሲሉ በጋዛ የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ አድናን አቡ ሃስና ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

ማሳሰቢያው የመጣው፣ በተባበሩት መንግሥታት የሚተዳደረው የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ምዕራፍ ምደባ፣ የጋዛ ከተማን እንዲሁም በደቡብ እና በማዕከላዊ ክልል የሚገኙ አካባቢዎች በረሃብ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በይፋ በማወጁ ነው፡፡

አድናን አቡ ሃስና አስቸኳይ ማሳሰቢያው "ዓለም በጋዛ ሰርጥ ስላለው ሁኔታ ያለውን አመለካከት እንደሚለውጥ እና የረሃቡን መስፋፋት ለመግታት እስራኤል መሻገሪያውን እንድትከፍት ያስገድዳታል" ብለው ተስፋ አድርገዋል፡፡

"ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ "በአሁን ወቅት ያለው የእርዳታ አቅርቦት በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ በቀን 600 የጭነት መኪናዎች እርዳታ መግባታቸውን ማረጋገጥ፣ መሻገሪያዎችን መክፈት እንዲሁም ምግብ፣ አቅርቦቶች፣ መስክ ሆስፒታሎች፣ መድኃኒቶች፣ ተጨማሪ አልሚ ምግቦች፣ ውሃ እና ነዳጅ እንዲገቡ መፍቀድ አስፈላጊ ነው፡፡"

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0