ሩሲያውያን የሰንደቅ ዓላማ ቀናንን በምድር እና በኅዋ ላይ አከበሩ
20:08 22.08.2025 (የተሻሻለ: 20:14 22.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያውያን የሰንደቅ ዓላማ ቀናንን በምድር እና በኅዋ ላይ አከበሩ
በዓለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ላይ የሚገኙ የሩሲያ ጠፈርተኞች፣ የሩሲያውያን የሰንደቅ ዓላማ ቀን መዘከራቸው የሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት "ከምድር ባሻገር ከፍ ማለታቸውን" አትጽናኦት የሰጠ ነው፡፡
ሰንደቅ ዓላማው በሩሲያ የሚገኙ "የ200 የሚጠጉ ሕዝቦችን አንድነት" እንዲሁም የሀገሪቱን "ትጋት፣ ጥንካሬ እና አንድነት" ያመለክታል ሲሉ ሩሲያዊው ጠፈርተኛ አሌክሲ ዙብሪትስኪ ተናግረዋል፡፡
የታሪካዊውን ባለሦስት ቀለም ሰንደቅ መመለስን ለመዘከር በ1994 የተጀመረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላው ሩሲያ በአርበኝነት ማሳያዎች ተከብሯል፡፡
በማሪዩፖል 2 ሺህ ስኩዌር ሜትር መጠን ያለው የሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ በከተማው መሃል ተውለብልቧል።
በሴንት ፒተርስበርግ 30 በ 50 ሜትር ስፋት ያለው የሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ በፒተር እና ፖል ግንቦች ላይ ተውለብልቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 
© telegram sputnik_ethiopia
/