የአሜሪካን እውቅና የምትጠባበቀው ሶማሊላንድ መሪ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲያሸንፉ ድጋፋቸውን ሰጡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካን እውቅና የምትጠባበቀው ሶማሊላንድ መሪ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲያሸንፉ ድጋፋቸውን ሰጡ
የአሜሪካን እውቅና የምትጠባበቀው ሶማሊላንድ መሪ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲያሸንፉ ድጋፋቸውን ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.08.2025
ሰብስክራይብ

የአሜሪካን እውቅና የምትጠባበቀው ሶማሊላንድ መሪ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲያሸንፉ ድጋፋቸውን ሰጡ

አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ፣ “እኔ እንደ ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንትነቴ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያጯቸውን የዓለም መሪዎችን መቀላቀሌን አውጃለሁ” ብለዋል፡፡

ይህ ድጋፍ እውቅና ያላገኘችው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ከዋሽንግተን ይፋዊ እውቅናን እና ሀገርነትን መሻቷ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

አብዱላሂ ትራምፕ ሪፐብሊኳን እውቅና የመስጠት እድል መኖሩን ማጤናቸው በማመስገን፣ ሶማሊላንድ እውቅና ለመሰጠት በኮንግረሱ የሕግ ረቂቅ በመተዋወቁ ድግሞ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎችን አውድሰዋል፡፡

የትራምፕ አስተዳደራቸው ለዓለም አቀፍ እውቅና ለረዥም ጊዜ ደጅ የጠናውን የሶማሊላንድ ጥያቄ “በትኩረት እያጤኑት” መሆኑን ከዚህ ቀደም ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0