የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የዘር ሐረግን የተቀላቀለችው ልዕልት ኤልያና
19:27 22.08.2025 (የተሻሻለ: 19:34 22.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የዘር ሐረግን የተቀላቀለችው ልዕልት ኤልያና
የንጉሡ የልጅ ልጅ ልጅ ልዕልት ኤድና ልዕልት ኤድና ተፈሪ መኮንን እና ጀማል ሮቢንሰን የልጃቸው ኤልያና ሮዝ መወለድን አብስረዋል፡፡
ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የተወለደችው ኤልያና የጥንዶቹ የመጀመሪያ ልጃቸው ናት፡፡ በኢትዮጵያውያን የዘር ሐረግ አቆጣጥር ሥራዓት መሠረት ንጉሠ ነገሥቱ የልዕልት ኤልያና ሮዝ “ቅማንት” ናቸው፡፡
ኤድና፣ "በራስ መተማመን እንዲኖራት እና ደግ ልብ ያላት ትሆን ዘንድ እሻለሁ፡፡ በርኅራኄ፣ በጉጉት እና በድፍረት የምትመራም እንድትሆልኝም እፈልጋለሁ።” ስትል ለልጇ ያላትን መልካም ምኞት ገልጿለች፡፡
ልጃቸው “ከነገሥታት እና ከንግሥቶች የዘር ሐረግ መምጣቷን፣ የቤተሰባችንን ታሪክ አስፈላጊነት እንድትረዳ” የማድረግ ኃላፊነት ከባለቤቷ ጋር እንደሚወስዱ መናገሯን የአሜሪካ መጽሔት አስነብቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
