ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ወሳኝ ሰነድ ማቅረቧን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ወሳኝ ሰነድ ማቅረቧን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የታሪፍ ሰነድ፤ ለነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራው ስኬታማነት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

"የታሪፍ ሰነዱ አስቀድሞ ለሴክሬታሪያት ቀርቧል፤ እናም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያትም ለአባል ሀገራቱ አሰራጭቶታል። በዚህ አግባብም በድረ-ገጹ ላይ ታትሟል። ይህም ግብይት ለመጀመር በጣም ወሳኝ ሰነድ ነው" ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን በይፋ ለመተግበር የሚያስችል ደንብ እንዳወጣች በቅርቡ ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡ ደንቡ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0