ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የመቻል ጥረትን ስታስቀጥል የበቆሎ ምርቷን በ37 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች
15:54 22.08.2025 (የተሻሻለ: 17:24 22.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የመቻል ጥረትን ስታስቀጥል የበቆሎ ምርቷን በ37 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የመቻል ጥረትን ስታስቀጥል የበቆሎ ምርቷን በ37 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች
የበቆሎ ምርትን ለማሳደግ ወሳኝ ንቅናቄ ያስጀመረው የግብርና ሚኒስቴር፣ በዚህ መኸር 160 ሚሊዮን ኩንታል ግብ አስቀምጧል፡፡
አርሶ አደሮች በመላ ሀገሪቱ 3.1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በቆሎ ተክለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2 ሚሊዮን ሄክታር አንጻር ከፍተኛ ጭማሪ አለው፡፡
የምርት ማሳደግ ዘመቻው የ36.75 በመቶ ምርት ጭማሪ ለማስገኘት የታሰበ ሲሆን፣ በስንዴ እና ሩዝ ዘርፎች ላይ በተገኙት የቅርብ ጊዜ ውጤቶች ላይ የተመሠረተ ነው ተብሏል፡፡
የመንግሥት ትኩረት፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች አቅርቦት እና የላቁ አሠራሮችን መተግበር ለበቆሎ ምርት እድገቱ ከፍተኛ አስዋታዖ ማድረጋቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ምስል ከግብርና ሚኒስቴር የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
