የሕክምና ቱሪዝምን ዒላማ ያደረገው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አግልግሎቱን ወደ ቀጣናው እያስፋፋ ነው
15:06 22.08.2025 (የተሻሻለ: 17:24 22.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሕክምና ቱሪዝምን ዒላማ ያደረገው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አግልግሎቱን ወደ ቀጣናው እያስፋፋ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሕክምና ቱሪዝምን ዒላማ ያደረገው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አግልግሎቱን ወደ ቀጣናው እያስፋፋ ነው
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የትምህርት ኃላፊ ዶክተር ሲሳይ ስርጉ፣ ወደ ውጭ ሀገር ለሕክምና የሚሄዱ ታካሚዎችን ለማስቀረት እና የጎረቤት ሀገራት ሕክምና ፈላጊዎች መጥተው እንዲታከሙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ኮሌጁ ለውጥኑ ስኬት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች፦
ዘመናዊ የልብ ሕክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል የሕንጻ ግንባታ፣
የጉበት፣ አንጀት እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ሕንጻ ግንባታ፣
ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እና ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ምርምሮችን በትብብር ማካሄድ፣
በምርምር፣ በሕክምና አገልግሎት እና በትምህርት አገልግሎት ከአጎራባች ሀገራት ጋር መሥራት
የሜዲካል ድህረ ምረቃ ትምህርት ከውጭ ለሚመጡ ተማሪዎች መስጠት፣
ሆስፒታሉ በጤና ትምህርት ዘርፍ ወደ 80 የሚጠጉ የሩዋንዳ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሱማሌ ላንድ ተማሪዎች በስፔሻላይዜሽን ደረጃ እያሰለጠነ ይገኛል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X