የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሚያገኙ ዜጎች መብቶችን ያስጠብቃል የተባለለት የሞባይል መተግበሪያ
12:22 22.08.2025 (የተሻሻለ: 17:24 22.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሚያገኙ ዜጎች መብቶችን ያስጠብቃል የተባለለት የሞባይል መተግበሪያ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሚያገኙ ዜጎች መብቶችን ያስጠብቃል የተባለለት የሞባይል መተግበሪያ
''ለመንገዴ'' የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በዓለም አቀፍ ሥራ ድርጅት ትብብር መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ነቢሃ መሐመድ፣ በኢትዮጵያውያን የበለጸገው "ለመንገዴ" የሞባይል መተግበሪያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን በማዘመን ዜጎች ከቅድመ ጉዞ ዝግጅት ጀምሮ በመዳረሻ ሀገራት እንግልት እንዳይገጥማቸው ጠቃሚ መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መተግበሪያ የሚከተሉትን ይዘቶች አካትቷል፦
የሥራ ስምሪት የሚወስዱ ዜጎችን መብትና ግዴታ፣
የአሠሪ እና ሠራተኛ የሥራ ግንኙነት፣
በመዳረሻ ሀገራት ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስል ቢሮዎች አድራሻ፣
የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማሠልጠኛ ተቋማትን፣ ምርመራ የሚሰጥባቸው የጤና ማዕከላት መገኛ፣
በሥራ ስምሪት ወቅት ችግር ቢገጥማቸው ለሚመለከተው አካል ጥቆማ መስጫ ይገኙበታል፡፡
የዓለም ሥራ ድርጅት የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ኩምቡላ ንዳባ፣ መተግበሪያው የዜጎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X