"ኢትዮጵያ የሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ ሁልጊዜ ሩሲያ ቀድማ ትመጣለች" - ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ
19:56 21.08.2025 (የተሻሻለ: 20:04 21.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ኢትዮጵያ የሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ ሁልጊዜ ሩሲያ ቀድማ ትመጣለች" - ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ
አንጋፋው ጋዜጠኛ እና የታሪክ አዋቂ ጥበቡ በለጠ፣ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1965 ዓ.ም የአገራቸውን ወታደራዊ ተቋማት ለማዘመን የጦር መሣሪያ ግዢ ለመፈጸም ወደ አሜሪካ አቅንተው ጥያቄቸው ተቀባይነት በማጣቱ ከፍተኛ ሐዘን ገጥሟቸው እንደነበር ያወሳሉ።
በወቅቱ ንጉሱ ከዋሺንግተን ወደ ሞስኮ ስለመቷት ስልክ እና ስለቀረበላቸው የ"ፈጥነው ይምጡ" ግብዣም ይተርካሉ።
"ጃንሆይ በጣም በሚገርም ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ አይደለም የተመለሱት፡፡ ወደ ሶቪየት ኅብረት ነው የሄዱት። የጠበቁት ሳይሆን ያልጠበቁት ከፍተኛ ድጋፍም አግኝተው ነበር የተመለሱት" ይላሉ።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ህልፈተ ሕይወት 50ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ያላቸውን ወንድማዊ ግንኙነት ዘክረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |