ግሎባላይዜሽን ምዕራባዊያንን መምሰል ማለት እንዳልሆነ ወጣቱን ማስገንዘብ ይገባል ተባለ

ሰብስክራይብ

ግሎባላይዜሽን ምዕራባዊያንን መምሰል ማለት እንዳልሆነ ወጣቱን ማስገንዘብ ይገባል ተባለ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አቅናው፣ ትውልዱ የራሱን ባሕል፣ ታሪክ እና የኑሮ ዘይቤ እንዲወድ እና እንዲጠብቅ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

"መንግሥት ኢትዮጵያን የሚመስሉ የኪነ ጥበብ እና የሥነ ጥበብ ውጤቶች እንዲበራከቱ ይበልጥ ዕድሎችን ማመቻቸት አለበት። ምዕራቡን ዓለም ከመምሰል አዙሪት ለመውጣትም የፈጠራ ሰዎች የራስን ሐብት በከፍተኛ ጥራት ማቅረብ ላይ በትኩረት ሊሠሩ ይገባል" ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ የትውልዱን ሰብዕና ወደ አገሩ ለመመለስ ሊሠሩ ይገባል ያሏቸውን ሌሎች ነጥቦችንም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0