17 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሕልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ አስታወቀ
16:31 21.08.2025 (የተሻሻለ: 16:34 21.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ17 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሕልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
17 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሕልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ አስታወቀ
በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ብቻ በዓይን ብሌን ጠባሳ ይሰቃዩ የነበሩ 51 ሕመምተኞች የዓይን ብርሃናቸው መመለሱንም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አምሳለ ጌታቸው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ከተመሠረተ 21 ዓመት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ፣ እስካሁን ለ3 ሺህ 600 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተካላ ቢያደርግም በሚጠበቀው ልክ ግን እንዳልሆነ ተጠቁሟል፡፡
አገልግሎቱ በሚፈለገው ደረጃ ያልተሰጠባቸው ምክንያቶችም ተጠቅሰዋል፦
የለጋሾች ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፣
የቴክኒሻኖች እና የቀዶ ሕክምና ባለሞያዎ እጥረት፣
የለጋሾች እና የተለጋሾች የቁጥር ልዩነት ከፍተኛ መሆን ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች የዓይን ብሌን ልገሳ እንዲደረግላቸው ተመዝግበው ተራቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙም ባንኩ ገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |