የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡጃ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡጃ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡጃ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡጃ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ

አየር መንገዱ ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ጀምሮ በንናምዲ አዚኪዌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መካከል በሳምንት ሦስት ተጨማሪ በረራዎችን በመጨመር የበረራ ድግግሞሹን ያሳድጋል፡፡

ከአቡጃ በየቀኑ የሚበርረው እና በሐምሌ 2025 የሌጎስ በረራውን በእጥፍ በማሳደግ በቀን ሁለቴ ያደረገው አየር መንገዱ፣ የናይጄሪያ ተጓዦች ፍላጎት መጨመሩን ገልጿል፡፡

ከጎርጎሮሳውያኑ 1960 ጀምሮ ናይጄሪያን በማገልገል ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በርካታ ከተሞችን ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር ያገናኛል፡፡

አዲስ የምሽት በረራዎች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ እና የኤስያ መዳረሻዎች ተስማሚ ግንኙነቶችን የሚያቀርቡ ሲሆን ለተሳፋሪዎች ተጨማሪ የሻንጣ ጭነቶች ፈቃድን ያካትታሉ፡፡

"እነዚህን ተጨማሪ ጥቅሞች ለታማኝ ተሳፋሪዎቻችን እየሰጠን ነው" ያሉት የናይጄሪያ የአካባቢ ሥራ አስኪያጅ ፍሬሕይወት መኮንን፣ የተጨመረው የጊዜ ሰሌዳ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የጉዞ ጊዜን ለመቀነስ ያለመ መሆኑን አክለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0