ዩክሬን ለግጭቱ ዘላቂ እና የረዥም ጊዜ እልባት ፍላጎት እንደሌላት በቀጥታ እያሳየች ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዩክሬን ለግጭቱ ዘላቂ እና የረዥም ጊዜ እልባት ፍላጎት እንደሌላት በቀጥታ እያሳየች ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
ዩክሬን ለግጭቱ ዘላቂ እና የረዥም ጊዜ እልባት ፍላጎት እንደሌላት በቀጥታ እያሳየች ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.08.2025
ሰብስክራይብ

ዩክሬን ለግጭቱ ዘላቂ እና የረዥም ጊዜ እልባት ፍላጎት እንደሌላት በቀጥታ እያሳየች ነው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

የሩሲያ እና የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ላቭሮቭ እና ጃይሻንካር በሞስኮ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰጧቸው ዋና ዋና መግለጫዎች፦

🟠 ሩሲያ በ2022 በኢስታንቡል ከስምምነት የተደረሰባቸውን የደህንነት ዋስትናዎች መርሆዎችን ትደግፋለች፣ ሌላው ነገር ትርጉም አልባ ድካም ነው፡፡

🟠 ሩሲያ ለዩክሬን የዋስትናዎች የጋራ አቅርቦት መርህን አግባብነት ያለው እንደሆነ ትመለከታለች።

🟠 በእውነቱ፣ አውሮፓ በዩክሬን ግዛት ውስጥ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሐሳብ እያቀረበች ነው፤ ይህ በሞስኮ ዘንድ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።

🟠 በዩክሬን ውስጥ የውጭ ወታደሮች ኑባሬ በሩሲያ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡

🟠 በሩሲያ እና አሜሪካ የአላስካ ስብሰባ፣ በዩክሬን ዙሪያ ያለውን ግጭት እልባት መስጠት በሚቻልባቸው አማራጮች እና መመዘኛዎች ብያኔ ላይ ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል፡፡

🟠 የዩክሬን አቋም ኪዬቭ የትራምፕን የእልባት ጥረቶች ማፋረስ እንደምትፈልግ ያሳያል፡፡

🟠 ወደፊት ከዩክሬን ጋር ስምምነቶችን የመፈራረሚያ ጊዜ ሲመጣ፣ በዩክሬን በኩል የሚኖሩ ፈራሚዎች ላይ የሕጋዊነት ጥያቄ ይነሳል፡፡

🟠 ላቭሮቭ፣ በዩክሬን ያለውን ሁኔታ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የማክሸፍ የአውሮፓ አካሄድ እንደሚከሽፍ እና ሩሲያ እና አሜሪካ መሪዎቻቸው እንደተስማሙት መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋ፡፡

🟠 ፑቲን ከዜሌንስኪ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ ውይይት የሚሹ ጉዳዮች በሙሉ በደንብ ከተሰናዱ ብቻ ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0