‘የተነሳሽነት ምንጭ’፤ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር የማሊን የባሕል ንቅናቄዎች አሞካሹ
13:16 21.08.2025 (የተሻሻለ: 13:24 21.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
‘የተነሳሽነት ምንጭ’፤ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር የማሊን የባሕል ንቅናቄዎች አሞካሹ
የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪምታልባ ዣን ኢማኑኤል ኡዌድራኦጎ ወደ ማሊ ባደረጉት የወዳጅነት እና የሥራ ጉብኝት፣ የባላ ፋሴኬ ኩያቴ መልቲሚዲያ የጥበባት እና የዕደ ጥበብ ማቆያን እና ብሔራዊ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
ሁለቱም ሀገራት በሳሕል ሀገራት ጥምረት ኮንፌዴሪሽን ውስጥ ከፖለቲካዊ እና የፀጥታ ትብብር ጎን ለጎን ባሕልን የውህደት ምሰሶ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡
ረቡዕ ኡዌድራኦጎ በማሊ ዜጎች ብርጌድ ሁለተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይም ተሳትፈዋል።
ለመኮንኖች፣ ለማኅበረሰብ መሪዎች እና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ባደረጉት ንግግር፣ ተነሳሽነቱ "የማሊ ወጣቶችን እና ማኅበረሰብን አስተሳሰብ ለመለወጥ ዘላቂ መሣሪያ" ነው ብለው ገልፀውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ