አሜሪካ በራሷ እና በእስራኤል ላይ እርምጃ ወስደዋል ባለቻቸው አራት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ በራሷ እና በእስራኤል ላይ እርምጃ ወስደዋል ባለቻቸው አራት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች
አሜሪካ በራሷ እና በእስራኤል ላይ እርምጃ ወስደዋል ባለቻቸው አራት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.08.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ በራሷ እና በእስራኤል ላይ እርምጃ ወስደዋል ባለቻቸው አራት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኪምበሪ ፕሮስት (ካናዳ)፣ በኒኮላስ ጊሎው (ፈረንሳይ)፣ በናዝሃት ሻሚም ካን (ፊጂ) እና በማሜ ማንዲያዬ ኒያንግ (ሴኔጋል) ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቀዋል።

ሩቢዮ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት "የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን፣ ሥልጣን አላግባብ መጠቀም፣ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ችላ ማለት እና ሕገ-ወጥ የፍትሕ ጣልቃገብነት" ምክንያት ማዕቀቡ እንደተጣለ ገልፀው፤ አሜሪካ ወታደሮቿን፣ ሉዓላዊነቷንና አጋሮቿን ለመጠበቅ እርምጃ እንደምትወስድ አሳስበዋል።

"አይሲሲ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ችላ ማለቱንና የአሜሪካና የእስራኤል ዜጎችን ለመመርመር፣ ለመያዝ፣ ለማሰርና ለመክሰስ ጥረቶችን በማድረግ ሕግን እንደ የጦር መሳሪያ መጠቀሙን ቀጥሏል... የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአሜሪካውያንና በእስራኤላውያን ላይ በሚወስደው...መሠረት ቢስ እርምጃ ተጠያቂ የሆኑትን አካላት ተጠያቂ ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ሲሉ በኤክስ የማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0