15 የኢትዮጵያ ከተሞች በዲጂታል አድራሻ ስርዓት ሊተሳሰሩ እንደሆነ ተገለፀ
17:14 20.08.2025 (የተሻሻለ: 17:24 20.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
15 የኢትዮጵያ ከተሞች በዲጂታል አድራሻ ስርዓት ሊተሳሰሩ እንደሆነ ተገለፀ
በኢትዮጵያ አድርሻን ከማግኘት ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ ችግሮች የአደጋ ግዜ ሥራዎችን ማከናወን አስቸጋሪ አየሆነ በመምጣቱ ከተሞችን በዲጂታል ሥርዓት ማስተሳሰር አስፈላጊ ሆኗል።
ሀገሪቱ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የዲጂታል ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እንደጀመረች የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
አገልግሎቱ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሆኗል። በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን እና ጅማ ታህሳስ 30፣ 2018 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሥራቸው የተጀመረው ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ ሚዛን አማን፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሽ ሰባት፣ ሃዋሳ፣ ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ዝርጋታቸው በ2018 የበጀት ዓመት ይጠናቀቃል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X