የዩክሬን የደህንነት ዋስትናዎች እንደ ቻይና፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ባሉ ሀገራት የእኩል ተሳትፎ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የዩክሬን የደህንነት ዋስትናዎች እንደ ቻይና፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ባሉ ሀገራት የእኩል ተሳትፎ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህን ያሉት ከዮርዳኖስ አቻቸው ሞስኮ ውስጥ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

የላቭሮቭ ተጨማሪ መግለጫዎች፦

🟠 ሞስኮ፤ ሩሲያ ራሷ ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና መስጠት አለባት በሚለው ሃሳብ ትስማማለች፣

🟠 ያለ ሩሲያ ተሳትፎ የሚደረጉ የደህንነት ዋስትና ውይይቶች፤ ብዙ መንገድ አያስኬዱም፣

🟠 ማክሮን በዩክሬን ግጭት ላይ የያዙት ጀብደኛ እና ግጭት አጫሪ አቋም አሁን ባለው የአሜሪካ አስተዳደር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፣

🟠 የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ካጃ ካላስ፤ ኅብረቱ ከሩሲያ ጋር የሚደረጉ ምንም አይነት ስምምነቶችን እንደማይፈቅድ የሰጡት መግለጫ አሳፋሪ የውጭ ፖሊሲ አካሄድ ነው፣

🟠 ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በሚደረገው ድርድር የልዑካን መሪዎችን ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሀሳብ አቅርባለች፣

🟠 በዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት ሩሲያ በማንኛውም መልኩ ለመሥራት ዝግጁ ናት፤ ነገር ግን የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባዎች የተሟላ ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0