“ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር የብሪክስ የተማከለ ማዕቀፍ እንዲፈጠር አጥብቃ ድጋፍ ታደርጋለች” - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል
12:46 20.08.2025 (የተሻሻለ: 12:54 20.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር የብሪክስ የተማከለ ማዕቀፍ እንዲፈጠር አጥብቃ ድጋፍ ታደርጋለች” - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር የብሪክስ የተማከለ ማዕቀፍ እንዲፈጠር አጥብቃ ድጋፍ ታደርጋለች” - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ከመስከረም 5-7 በብራዚል መዲና ብራዚሊያ በሚካሄደው ሁለተኛው የብሪክስ “ባሕላዊ እሴቶች” ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡
በጉባኤው የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ባሕላዊ እሴቶችን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን በመጠበቅ ረገድ የሚኖረውን ሚና በተመለከተ ሪፖርትም ያቀርባሉ፡፡
“በዚህ ፈጣን የቴክኖሎጂ ዕድገት ዘመን፤ በተለይም ብሪክስ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ ተገቢው ቁጥጥር እንዲደረግ ጥረቶችን በማስተባበር ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ የተቀናጀ ትብብር እና ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት የጋራ መመዘኛ መፍጠር ካልተቻለ ባሕላዊ እሴቶችን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን መጠበቅ አይቻልም" ሲሉ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ከጉባኤው በፊት ተናግረዋል፡፡
◻ ሁለተኛው የብሪክስ “ባሕላዊ እሴቶች” ጉባኤ የፓርላማ አባላትን፣ ታዋቂ የመንግሥት እና የባሕል ግለሰቦችን እንዲሁም የብሪክስ አባላት እና አጋር ሀገራት የንግድ ተወካዮችን ያሰባስባል፡፡
ጉባኤው በሥነ-ምግባር፣ ቴክኖሎጂ እና የሰብዓዊ አጋርነት ዘርፎች በጋር እሴቶች ላይ የተመሠረተ ምክክር እና ትብብር ለማዳበር ያለመ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X