የናሚቢያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ቤተሰቦች ጀርመንን ከሰሱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናሚቢያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ቤተሰቦች ጀርመንን ከሰሱ
የናሚቢያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ቤተሰቦች ጀርመንን ከሰሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.08.2025
ሰብስክራይብ

የናሚቢያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ቤተሰቦች ጀርመንን ከሰሱ

ቤተሰቦቹ እ.ኤ.አ በ2021 በናሚቢያ እና በጀርመን መንግሥት በተደረሰው ስምምነት ድምጻችን አልተካተተም በማለት የሕግ እርምጃ ወስደዋል፡፡

አሁናዊ ሁኔታ፦

ጀርመንን ለፍርድ ለማቆም በመጪው ጥቅምት 17 በናሚቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ ይሰማል፡፡

ታሪካዊ ዳራ፦

እ.አ.አ ከ1904 እስከ 1908 የጀርመን ቅኝ አገዛዝ ኃይሎች በሄሬሮ እና ናማ ሕዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል። ለብዙ አሥርተ ዓመታት ጀርመን ለይፋዊ የካሳ ጥያቄዎች ምላሽ ላለመስጠት ስትከላከል ቆይታለች።

የ2021 ስምምነት፦

ጀርመን በስተመጨረሻም ታሪካዊ በሆነው ውሳኔ፦

▪የተፈፀሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች “ከወቅታዊ እይታ አንፃር” የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆኑ አምናለች።

▪በይፋ ይቅርታ ጠይቃለች።

▪በ30 ዓመታት ውስጥ የሚከፋፈል 1.3 ቢሊየን ዶላር የልማት እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብታለች።

የክሱ መነሻ፦

የሰለባዎቹ ቤተሰቦች ስምምነቱን ውድቅ አድርገዋል። የሚከተሉትንም በምክንያትነት ያቀርባሉ፦

▫የእርዳታ ገንዘቡ ይፋዊ የ "ካሳ ክፍያ" ባለመሆኑ ወንጀሉን በአግባቡ አልካሰም።

▫ የናሚቢያ መንግሥት ጉዳት ከደረሰባቸው ማሕበረሰቦች ጋር በአግባቡ አልተማከረም።

▫ መግለጫው የተሰጠው ያለነሱ ፈቃድ ነው።

ክሱ የስምምነቱን ሕጋዊነት በመቃወም ለታሪካዊ ጥፋቶች የተሻለ ፍትሐዊ መፍትሄ ለማግኘት ያለመ ነው።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀግ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0