ሩሲያ ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች
18:03 19.08.2025 (የተሻሻለ: 18:04 19.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች
የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ከኢትዮጵያ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ጋር የበየነመረብ ውይይት ባደርጉበት ወቅት የሞስኮን ድጋፍ አረጋግጠዋል፡፡
"የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት በውይይቱ ተነስቷል። የሩሲያ ወገን የኢትዮጵያን እቅዶች ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ እና የቴክኒክ እና የማማከር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል" ሲል የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ሬሼትኒኮቭ የሩሲያና ኢትዮጵያ የንግድ ልውውጥ መጠን እያደገ መሄዱንም ጠቁመዋል። እ.ኤ.አ በ2025 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ2.2 ጊዜ ጨምሮ 191.2 ሚሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል።
ሩሲያ በዋናነት ከኢትዮጵያ የቡና ምርት እያስገባች እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/