“የዓለምአቀፋውያን ፍላጎት የዩክሬንን ግጭት ማስቀጠል ነው” - ባለሙያው
16:21 19.08.2025 (የተሻሻለ: 16:24 19.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“የዓለምአቀፋውያን ፍላጎት የዩክሬንን ግጭት ማስቀጠል ነው” - ባለሙያው
“የዩክሬንን ቀውስ በገንዘብም ሆነ በጦር መሳሪያ በማቅረብ እያባባሱ ያሉት እነሱ በመሆናቸው፤ ለዓለምአቀፋውያን ያደሩ የአውሮፓ ልሂቃን ሰላምን እንደ የተሻለ አማራጭ እንዲቀበሉ ማሳመን ቀላል ይሆናል ብዬ አላምንም” ሲሉ የሰርቢያ ፓርላማ አባልና ወታደራዊ ምሁር ሚታር ኮቫች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ምሁሩ እንደሚያምኑት የግሎባሊስቶች እውነተኛ ዓላማ በሩሲያ ላይ ወታደራዊ ድልን ማግኘት ነው።
ኮቫች አክለውም አሜሪካ በቀድሞው የባይደን እና ባልደረቦቻቸው ስትራቴጂ ከመመራት መቆጠቧ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ትራምፕ በአሜሪካና በአውሮፓ ግሎባሊስት ልሂቃን ጫና ሊደረግባቸው እንደሚችል ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጫና መቋቋም እንደሚችሉ እምነታቸውን ገልፀዋል።
ኮቫች የፑቲን እና የትራምፕ ጉልህ ስልታዊ እርምጃዎች መተማመንን የሚያጎለብቱ እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለሙ ይሆናሉ ብለዋል።
እንደ ኮቫች ገለጻ ማንኛውም ስምምነት ሩሲያ ከቀውሱ በፊት ያስቀመጠቻቸውን ቅድመ ሁኔታዎች መቀበልን ይጠይቃል፦
🟠 የዩክሬን ገለልተኝነት፤
🟠 በግዛቷ ላይ የውጭ ወታደራዊ ኃይል እንዳይሰፍር ክልከላ መጣል፣
🟠 የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ዩክሬን የኔቶ አባል እንዳትሆን ማገድ ናቸው።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X