ከአውሮፓ መሪዎች ጋር በተደረገው ውይይት የትራምፕ እና ዘለንስኪ ቁልፍ መግለጫዎች፦

ከአውሮፓ መሪዎች ጋር በተደረገው ውይይት የትራምፕ እና ዘለንስኪ ቁልፍ መግለጫዎች፦
ትራምፕ፦
የዩክሬንን ግጭት መፍታት እንደሚቻል በ "አንድ ወይም ሁለት ሳምንት" ውስጥ ይታወቃል።
እስካሁን በኋይት ሃውስ የተካሄዱት ዝግጅቶች በጣም በተሳካ ሁኔታ መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ከአውሮፓ ኅብረት መሪዎች እና ከዘለንስኪ ጋር የሚኖራቸው ስምምነት ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ የሶስትዮሽ ውይይት ይመራል ብለው ይጠብቃሉ።
በአላስካው ጉባኤ ፑቲን ሩሲያ ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና እንደምትሰጥ ተስማምተዋል።
ከአውሮፓ ኅብረት መሪዎች እና ከዘለንስኪ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በግዛቶች ልውውጥ ዙሪያ እንደሚመክር ተናግረዋል።
የሩሲያ እና ዩክሬን የግዛት ልውውጥ ውይይት የጦር
ግንባሩን "አሁናዊ የግንኙነት መስመር" ግምት ውስጥ ይከታል።
ቀጣዩ እርምጃ የሶስትዮሽ ስብሰባ መሆኑን ተናግረዋል። ፑቲን እና ዘለንስኪ በሰላማዊ መፍትሄ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ እምነታቸውን ገልጸዋል።
ከአውሮፓ ኅብረት መሪዎች እና ከዘለንስኪ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ደህንነትን ጨምሮ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ስምምነቶችን ይጠብቃሉ።
ዩክሬን ላይ ሊፈፀም የሚችል ወረራ "ከመጠን በላይ ተጋኗል" ብለው እንደሚቆጥሩ ገልጸዋል።
የዩክሬንን ደህንነት የሚያረጋግጥ ስምምነት ላይ ይደረሳል ብለው ያምናሉ።
ትራምፕ ስምምነት ላይመጣ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ዘለንስኪ፦
የግዛት ጉዳዮች በሶስትዮሽ ስብሰባ ላይ ውይይት ይደረግባቸዋል።
ከትራምፕ ጋር የተደረገውን ውይይት "በጣም ጥሩ" በማለት፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X