በትራምፕ እና ዘለንስኪ የኋይት ሃውስ ስብሰባ
21:15 18.08.2025 (የተሻሻለ: 21:24 18.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በትራምፕ እና ዘለንስኪ የኋይት ሃውስ ስብሰባ
የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
ትራምፕ፦
ከዘለንስኪ እና ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ከተገናኙ በኋላ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት "ጥሩ እድሎች" እንዳሉ ተናግረዋል።
ፑቲን እና ዘለንስኪ የዩክሬንን ግጭት ማቆም ይፈልጋሉ።
የአውሮፓ መሪዎችም የዩክሬንን ሰላም እንደሚሹ ገልጸዋል።
በሰላም እልባቱ መሠረት ለዩክሬን "የተሻለ ዋስትና" ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
የዩክሬን ግጭት እንዲቆም ተዋጊዎቹም እና መላው ዓለም የሚመኘው ነው በማለት ይህ የሚሆንበትን ግዜ ግን አሁን ላይ ለማወቅ እንደማይቻል ገልፀዋል።
ከዘለንስኪ እና ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ያሚያደረጉት ስብሰባ የመጨረሻ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የዩክሬን ሰላም ዘላቂ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ኔቶ ለዩክሬን የሚቀርበውን የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ወጪ እንደሚሸፍን ገልፀዋል።
ዘለንስኪ፦
ለግዛት ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም።
በዩክሬን ምርጫ ማድረግን በተመለከተ "የደህንነት ሁኔታዎች" እንደሚያስፈልጉ ተናግሯል።
ኪዬቭ የአሜሪካን የጦር መሳሪያ በመግዛት ረገድ ችግሮች አየገጠሟት እንደሆነ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X